ETC News
CORPORATE MESSAGE
WHO IS WHO
CHECK MAIL
VACANCY
YELLOW PAGES
FEEDBACK
FAQs
Dialing Codes
Interurban Dialing Code
Essential Numbers
International Dialing Codes
Websites at Ethiopage
Websites at ETC
-------------------------
Commercial websites
Educational websites
Govt. websites
NGO websites
Back to news page
Print
ኮርፖሬሽኑ የሞባይል ደንበኞች የሞባይል ኢንተርኔት GPRS አገልግሎትን በነጻ ማስጀመር እንዲችሉ አደረገ፡፡
July 12, 2010
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የሞባይል ኔትወርክን በመጠቀም የድምፅ፣ የተንቀሳቃሽ ምስል እና የፅሁፍ መልዕክቶችን ለመቀበልና ለማስተላለፍ የሚያስችለው የሞባይል ኢንተርኔት ወይም የGPRS አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኔትወርክ ማስፋፋት ሥራ ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት 2.146 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የድህረ እና የቅድመ ክፍያ የሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በነጻ ማስጀመር ወይም activate ማድረግ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡  
ሆኖም የGPRS አገልግሎትን ለማግኘት ደንበኞች የ2G እና ከዚያ በላይ የሆነ የሞባይል ቀፎ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን ቀፎዎቹ ውስጥ ኮንፊገር ለማድረግ የሚያስችሉት APN ወይም የWAP ምርጫ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 የጂፒ አር ኤስ አገልግሎትን በሞባይል ቀፎ ላይ ለማግኘትና ለመጠቀም
 ወይም configure ማድረግን በተመለከተ፡-
የGPRS አገልግሎትን ለማግኘት ሁለት ዓይነት የሞባይል ቀፎ አጠቃቀም configuration መንገዶች አሉ፡- እነሱም፡-
1. የደንበኛው የሞባይል ቀፎ Access Point Name ካለው etc.com የሚለውን በማስገባት የGPRS አገልግሎትን ማስጀመር /activate/ ማድረግ፣
2.    የደንበኛው የሞባይል ቀፎ APN ሳይሆን WAP ከሆነ “የWAP አገልግሎት ሰጪ” የሚለው አድራሻ ላይ በማስገባት የGPRS አገልግሎትን ማስጀመር activate ማድረግ ይቻላል፡፡
የጂፒ አር ኤስ አገልግሎት አጠቃቀም GPRS configuration በተለያዩ የሞባይል ቀፎዎች ላይ የተለያየ ሲሆን፣ የሚከተሉትን አራት ዓይነት የሞባይል ቀፎዎችን በምሳሌ በማስቀመጥ የአገልግሎቱን አጠቃቀም ማየት ይቻላል፡፡  
1ኛ. በሶኒ ኤሬክሰን Sony Ericsson የሞባይል ቀፎ
 በቅድሚያ ወደ ዋናው ማውጫ /menu/ በመግባት “Configuration” የሚለውን ቁልፍ መጫን፣  
 ቀጥሎ ወደታች በመውረድ “Connectivity” የሚለውን ቁልፍ መጫን፣
 ከዚያም “Data Communication” የሚለውን መምረጥ፣
 ቀጥሎም “Data Communication” በሚለው ማውጫ ስር “Data account” እና “Prefered Service” የሚሉትን ምርጫዎች ያገኛሉ፡፡
 ከዚያም “Preferred Service”  ከሚለው ምርጫ ውስጥ “PC and CS” የሚለውን መምረጥና “Data account” የሚለውን ምርጫ በመጫን “new account” የሚለውን መምረጥ የሚገባ ሲሆን፣ በመቀጠልም ወደ ታች በመውረድ “PS data” የሚለውን መጫን ያስፈልጋል፡፡
 ተገልጋዩ “PS Data” የሚለውን ከተጫነ በኋላ “GPRS” የተሰኘው የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጠው ምርጫ ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡
 በመጨረሻም “APN”ን በመጠቀም ኢንተርኔት ለማግኘት “etc.com” የሚለውን ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
2ኛ. በኖኪያ Nokia-Series ሞባይል ቀፎ አጠቃቀምን በተመለከተ፡-
    ወደ ዋናው ማውጫ /menu/ ውስጥ በመግባት ቁልፉን በመጫንና ወደታች በመውረድ “setting” የሚለውን መምረጥ፣
    ቀጥሎም ወደታች በመውረድ “Connectivity” የሚለውን ቁልፍ በመምረጥ “Chosen” የሚለውን መጫን፣
    ከዚያም “packet data GPRS” የሚለውን በመምረጥ ወደታች መውረድና “Packet data setting” የሚለውን ምርጫ መጫን፣
    ተገልጋዩ “Packet data setting” የሚለው አስተካክሎ ከጨረሰ በኋላ ወደ ሌላ ምርጫ ለመሄድ ቁልፉን መጫን ይኖርበታል፡፡
    ከዚያም “edit active access point” የሚለውን መርጦ መጫንና ማስተካከል ወይም edit ማድረግ፣
    “Packet data access point” የሚለውን በመክፈት የአገልግሎት ሰጪውን አድራሻ ማለትም “APN etc.com” የሚለውን በመጻፍ ማስገባትና የጂፒ አር ኤስ አገልግሎትን ማግኘት ይቻላል፡፡
3ኛ. በሳጌም Sagem OT 290 የሞባይል ቀፎ አጠቃቀምን በተመለከተ፡-
 ወደ ዋናው ማውጫ በመግባት “wap profiles” የሚለውን መምረጥ፣
 ቀጥሎም “advanced” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደሚቀጥለው መሄድ፣
 ከዚያም ተገልጋዩ “setting” የሚለውን ከተጫነ በኋላ ወደታች በመውረድ “provide” የሚለውን ከ”displayed providers” ማውጫ ውስጥ መምረጥ ይኖርበታል፡፡
 “provide” የሚለው ከተመረጠ በኋላ በቀፎው ስክሪን የቀኝ ጠርዝ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች ውስጥ
  ተገልጋዩ “GPRS” የሚለውን ከመረጠ በኋላ “wap profiles” የሚለውን ምርጫ ይመርጣል፤ ቀጥሎም “10.185.55.133”ን ካስገባ በኋላ ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡
የኢንተርኔት ሆም ፔጅ Homepage ሲመጣ “google”፣ “Yahoo” የሚለውን አንደኛውን በመምረጥ መጠቀም፣
ከዚያም “preffered connection” በሚለው ውስጥ በመግባት “GPRS”ን በመምረጥ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል፡፡
4ኛ. በሳምሰንግ Samsung ሞባይል ቀፎ አጠቃቀምን በተመለከተ፡-
 ተገልጋዩ ዋናውን ማውጫ በመጫን “fun box” የሚለውን ከመረጠ በኋላ “wap browser” የሚለውን ይጫናል፡፡
 ቀጥሎም  “wap browser” ከሚለው ማውጫ ወይም ዝርዝር ውስጥ አንዱን ወይም ማንኛውንም ምርጫ መምረጥ፣
 “WAP” የሚባለውን የAPN ስም በመጠቀም የ“GPRS”ን አገልግሎት ለማግኘት ወይም activate ለማድረግ “Setting” የሚለውን ምርጫን መጫን፣
 በመጨረሻም “10.185.55.133” የሚለውን የአገልግሎት ሰጪ ወይም የኮርፖሬሽኑ አድራሻ በመምረጥ የጂፒ አር ኤስ አገልግሎትን ማግኘት ይቻላል፡፡
የGPRS አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ተጨማሪ ጉዳዮች
   
•    የGPRS አገልግሎትን የሞባይል ስልክ ቁጥር በማስገባት አይሠራም፤ በምትኩ የአክሰስ ፓይንት ኖድ APN ይጠቀማል፡፡
•    የአከፋፈል ሥርዓቱ በጊዜ ቆይታ per minute ሳይሆን ደንበኞች በላኩት እና በተቀበሉት የዳታ መጠን በኪሎ ባይት ተሰልቶ የሚከፈል ሲሆን ለ100 ኪሎ ባይት 4አራት ሳንቲም እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
•    የGPRS አገልግሎት በዋየርለስ አክሰስ ኘሮቶኮል WAP አማካይነት ዳታዎች ለማስተላለፍ የሚያስችል ነው፡፡
•    የGPRS አገልግሎት ፍጥነት በተለያዩ ጉዳዮች የሚጨምር እና የሚቀንስ ቢሆንም ለአንድ ደንበኛ ሲሰጥ ከፍተኛው እስከ 21.4 kbs ድረስ አቅም ያለው ዳታ የማስተላለፍ ብቃት ይኖረዋል፡፡  
•    የGPRS አገልግሎትን ለመጠቀም ደንበኞች የሚጠቀሙበት የሞባይል ቀፎ ይህን አገልግሎት ሊሠጥ የሚችል GPRS enabled የሆነ የቀፎ ዓይነት መሆን ይኖርበታል፡፡
የGPRS አገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች እና መፍትሔዎችን በተመለከተ፡-
   
1.የአገልግሎት መቋረጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ
     
•    ሲም ካርዱ ለዳታ አገልግሎት ዝግጁ መደረጉን ማረጋገጥ እና በGPRS አማካኝነት ለሚደረግ ግንኙነት ተገልጋዩ አካውንቱ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2. የተሳሳተ አገልግሎት አጠቃቀም በሚያጋጥምበት ጊዜ፡-
•    ኢ-ሜይል መቀበል ነገር ግን መላክ የማያስችል ሁኔታ የሚያጋጥመው ተገልጋዩ የተሳሳተ የጂፒ አር ኤስ አክሰስ ፓይንት ሲጠቀም ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የጂፒ አር ኤስ መቀበያዎች ከአገልግሎት ሰጪው ኔትወርክ መውጫና መግቢያ ጋር እንዲገናኙ ተደርጎ በ“WAP” የሚሰሩ ናቸው፡፡ ይህ አሠራርም  ከመደበኛው የኢንተርኔት ድረገጽ ውጪ አስፈላጊ የዜና ይዘት ያላቸውን ገጾች ተገልጋዩ ፈልጎ browse ለማግኘት የሚያስችለው ሲሆን የመደበኛውን ኢንተርኔት አገልግሎት ሲፈለግ ግን የጂፒ አር ኤስ መቀበያውን ከኢንተርኔት ኤ ፒ ኤን APN ኔትወርክ ጋር እንዲገናኝ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116612997 ደውለው ይጠይቁ፡፡
Ethiopian Telecommunications Corporations
Copyright© 2009 Ethiopian Telecommunications Corp. All rights reserved!