ኮርፖሬሽኑ በሞባይል የኢንተርኔት GPRS አገልግሎት ላይ ታሪፍ ማሻሻያ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የሞባይል ኔትወርክን በመጠቀም የድምፅ፣ የተንቀሳቃሽ ምስል እና የፅሁፍ መልዕክቶችን ለመቀበልና ለማስተላለፍ የሚያስችለው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማለትም የGPRS አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ለመላው ህብረተሰብ በተመጣጠነ ዋጋ በማዳረስ በመረጃ የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር በሚያደርገው የዘውትር ጥረት  በሚቀጥለው ትውልድ Next Generation Network ቴክኖሎጂ በሞባይል ስልክ አማካይነት ደንበኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ከኢንተርኔት ድረ ገጾች ላይ የሚፈልጉትን መረጃዎች ማየትና ማንበብ እንዲሁም ምስል፣ ሙዚቃና የተለያዩ ፋይሎችን መገልበጥ down load እና የኢ-ሜይል አገልግሎትን ማግኘት እንዲችሉ  የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ አድርጓል፡፡  
ኮርፖሬሽኑ የሚሰጠው የGPRS አገልግሎት እስከ 21.4 ኪሎ ባይት በሰከንድ ድረስ ያለ ዳታ ወይም መረጃ የማስተላለፍ አቅም ያለው ነው፡፡
የተሻሻለው ታሪፍ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
• ለድህረ ክፍያ የሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን የማስጀመሪያ ክፍያ activation fee ቀድሞ እንደነበረው በነጻ የሚቀጥል ሲሆን ቀደም ሲል አንድ ሳንቲም በ1 ኪሎ ባይት የነበረው የአገልግሎት መጠቀሚያ ዋጋ አራት ሳንቲም በ100 ኪሎ ባይት  እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ከቀድሞው ታሪፍ ጋር ሲነፃፀር የ96  በመቶ ማሻሻያ መደረጉን ያሳያል፡፡
• ለቅድመ ክፍያ የሞባይል ተጠቃሚዎች ደግሞ አገልግሎቱን ለማስጀመር በነጻ ሲሆን አንድ ሳንቲም በ1 ኪሎ ባይት የነበረው የአገልግሎት መጠቀሚያ ዋጋ አራት ሳንቲም በ100 ኪሎ ባይት  እንዲሆን ተደርጓል፡፡
o በቅድመ ክፍያ ተጠቃሚነት ለታክስ ማሰባሰብ ሥራ የሞባይል GPRS አገልግሎትን ለሚጠቀሙ የአገልግሎቱ ማስጀመሪያ ቀድሞ በነበረው መልክ በነጻ እንዲቀጥልና በተመሳሳይ አንድ ሳንቲም በ1 ኪሎ ባይት የነበረው የአገልግሎት ዋጋ አራት ሳንቲም በ100 ኪሎ ባይት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የGPRS አገልግሎት ታሪፍ እንደአስፈላጊነቱ ለወደፊት ሊሻሻል የሚችል ሲሆን ቀደም ሲል የነበረውና የአሁኑ የዋጋ ዝርዝር ሰንጠረዥ በማነፃፀር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
 
|
 
የአገልግሎት ዓይነት |
አገልግሎት ለማስጀመር activation fee  /በብር/ |
የአገልግሎት ክፍያ
service charge
/በሣንቲም/ |
 
መግለጫ |
|
የቀድሞ ታሪፍ |
የአሁኑ ታሪፍ |
የቀድሞ ታሪፍ |
የአሁኑ ታሪፍ |
|
ቅድመ ክፍያ |
45.00 |
ነጻ |
1/KB |
4/100KB |
ለሁሉም ደንበኞች |
|
ቅድመ ክፍያ |
ነጻ |
ነጻ |
1/KB |
4/100KB |
ለታክስ መሰብሰብ /አጠቃቀም |
|
ድህረ ክፍያ |
ነጻ |
ነጻ |
1/KB |
4/100KB |
ለሁሉም ደንበኞች |
ማስታወሻ፡-
• ከላይ በሰንጠረዥ የተገለፀው ዋጋ ተ.እ.ታ አይጨምርም፡፡
• ከላይ የተቀመጠው ታሪፍ ለመላክ እና ለመቀበል የሚያገለግል ይሆናል፡፡
• ሽርፍራፊ ፍጆታዎች ወደ ሚቀጥለው KB ተጠጋግቶ ሂሳቡ ይሰላል፡፡ 
የGPRS አገልግሎትን ለማግኘት ደንበኞች የ2G እና ከዚያ በላይ የሆነ የሞባይል ቀፎ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን ቀፎዎቹ ውስጥ ኮንፊገር ለማድረግ የሚያስችሉት APN    ወይም የWAP ምርጫ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
የGPRS አገልግሎት ለድህረ ክፍያ post paid  እና ለቅድመ ክፍያ pre paid የሞባይል ተጠቃሚዎች  መሰጠት ጀምሯል፡፡
ጥር 6 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን